የፓስተር መልእክት

እንኳን ወደ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን በደህና መጣችሁ! በቤተ ክርስቲያናችን፣ ሁሉም ሰው በእምነት የሚያድግበት፣ ድጋፍ የሚያገኙበት እና የእግዚአብሔርን ፍቅር የሚለማመዱበት ቤተክርስቲያን ናት።
በቤተ ክርስቲያናችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ተስፋን፣ ፈውስን፣ ወይም ጥልቅ ግንኙነትን የምታደርጉበት ቤታችሁ ነው፡
እኛ በእግዚአብሔር ቃል እና እውነት ላይ የተመሰረተ እና በዕለት ተዕለት ህይወት ወንጌልን እንድንኖር በመንፈስ ቅዱስ ሃይል የተሰጠን የወንጌላውያን ነን። በእግዚያብሔር መንፈስ እናመልካለን፣ በደስታ እንመሰክራለን፣ እናም አብረን በእምነት እንጓዛለን። ከእሁድ አምልኮ ጀምሮ እስከ ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች፣ የህጻናት አገልግሎት መስጫ ፕሮግራሞች፣ የምናደርገው ነገር ሁሉ ሰዎችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ—ሕይወት እንድትመጡ መጋበዝ ነው።
ለእምነት አዲስ ከሆኑ ወይም ከረጅም ጊዜ ርቀው ከተመለሱ፣ እንደገና ለመጀመር ምንም የተሻለ ቦታ የለም። ሁላችሁም እንድትመጡ እና በክርስቶስ በዓላማ፣ በሰላም እና በኃይል መኖር ምን ማለት እንደሆነ እንድታውቁ በአባታችን በእግዚያብሔር በመዳኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በተሰጠን ፍቅር እናንተንም ወደአማኑኤል ቤተክርስቲያን ከተስፋው ቃል ተካፋይ እንድትሆኑ እንጋብዛቹሀለን፡፡
ዮሐንስ 3፡16
” በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”
የቤተክርስቲያናችን ማስታወቂያዎች
Church
events
Summer Camp
Family Conference
Picnic
Young Adult service
የጸሎት አገልግሎት
ቤተክርስቲያንን፣ ማህበረሰብን እና ግለሰቦችን በምልጃ ጸሎት መርዳት።


